Saturday, March 29, 2014

የመቐለ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በየካቲት 11 ስም በተዘጋጀው በአል ለመገኘት ታስቦ የህወሃት አባላትና ካድሬዎች ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ እንዳስፈራሩትና እንዳስገደዱት የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በየካቲት 11 በአል ላይ እንዲገኙ ለማስገደድ ተብሎ በጥቅም የተደለሉ የስርአቱ አባላት እና ካድሬዎች ከየካቲት 10 / 2006 ዓ/ም ጀምረው ቤት ለቤት እየዞሩ ሃይለ ቃል በመጠቀም ላስተላለፉት ትእዛዝ ህዝቡ ስላልተቀበለው በበአሉ ዕለት ሰልፍ ይዞ ወደ ሰማእታት ሃወልት ይጓዝ የነበረ ህዝብ ከመቐለ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ብዛት ሲነፃፀር ከ2-3 ሺ እንደማይበልጥ ለማወቅ ተችለዋል።
   ከአሁን በፊት ህዝብ ወደ ሰማእታት ሃወልት ሲገባ ተደርጎ በማይታወቅ መንገድ ሰልፈኛው በፈደራል ፖሊስ እየተፈተሸ እንዲገባ እንደተደረገና በበአሉ ምክንያት ከአኽሱም ሆቴል እስከ ሰማእታት ሃወልት ለእግረኛ ዝግ እንዲሆን በመደረጉ ምክንያት ህዝቡ ወደ ሚካኤል ቤተክርስትያን በሚወስደው መንገድ ተጠቅሞ እንዲጓዝ ስለ ተደረገ ላልተፈለገ ድካምና እንግልት ተጋልጠዋል ሲል መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።
   በበአሉ ቀን የመቐለ ከተማ መንገዶች ከየት እንደመጡ በማይታወቁ የፈደራል ፖሊስ አባላት ተጥለቅልቆ እንደዋለ የጠቆመው መረጃው በአሉ እየተካሄደበት ከነበረ የሃወልቲ አካባቢ ዉጭ ሲንቀሳቀስ ለተገኘ ሰው ልትሰርቅ ፈልገሃል፤ ኣሸባሪ ነህ ወዘተ በሚሉ ሰንካላ ምክንያቶች ህዝቡን ስላስቸገሩት ናዋሪው በአሉ እስኪያልፍ ድረስ  በቤቱ ውስጥ ተዘግቶ እንዲውል መገድዱ ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድተዋል።