Saturday, March 29, 2014

በዛሬማ ወረዳ ለሚኖር ህዝብ ተቃዋሚዎችን ትተባበራላቹህ፤ ትደግፋላቹህ በሚል ምክንያት በስርአቱ የፈደራል ፖሊስ አባላት የንግድ ተቋማቸው እየዘጉባቸውና እያንገላትዋቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዛሬማ ከተማ ውስጥ ለሚገኝ ህዝብ በፀጥታ አስከባሪዎች ስም የተሰማሩ የፈደራል ፖሊስ አባላት አሸባሪዎች እና ተቃዋሚዎች ትደብቃላቹህ በሚል ምክንያት ህጋዊ ባልሆነ መንገድ መኖሪያ ቤታቸውና ተቋማቸው ሌት ተቀን በመፈተሽ ህዝቡን እያበሳበሱት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል።
    የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የፈደራል ፖሊስ አባላት። በተለይ በንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ዜጎች በሚያካሂዱት ፍተሻ ለባለንብረቶቹ በማስፈራራትና በማባረር ንብረታቸው እንደዘርፍዋቸውና በርከት ያሉ ተቋማት እንደታሸጉ ታውቋል።
   ንብረታቸው ከተወሰደባቸው ዜጎች መሃል አቶ ትንሳኤ ፈንቴ፤ ሽመት ታደገ፤ ተፈራ ኣብሆይንና ኣቶ ቀርበህ በዛብህ የተባሉ የሚገኙባቸው የወርቅ ቤት ማሽንና ሚዛን እንደተወሰደባቸው የገለፀው መረጃው እነዚህ ወገኖችም ድርጅታቸው ከተዘጋ በኋላ አማርረው ወደ ሌላ አከባቢ ለቀው እንደሄዱ ለማወቅ ተቸለዋል።