Saturday, March 15, 2014

በአማራ ክልል አዊ ዞን አንከሻ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የትምህርት ክፍል ሃላፊዎች የሃገርና የህዝብ ገንዘብ እያጠፋፉት መሆናቸው ተገለፀ።



የህዝቡን ገንዘብ እያጠፋፉ ያሉ የወረዳው የትምህርት ክፍል ሃላፈዎች የቀን አበል እያወጣን ነን በሚል ምክንያት በጥርና በየካቲት 2006 ዓ/ም ብቻ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከ200ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ገንዘቡን እንዳጠፋፉት የገለጸው መረጃው በእንደዚህ ዓይነት የሙስና ተግባር ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙ ሃላፊዎቹም በአገው ትምህርት ቤት ግምጃ ቤት ቁጥር 1 ውስጥ የሚሰሩ እንደሆኑ ተገልፀዋል።
     ገንዘቡን ካጠፋፉት ግለሰቦች ስም ለመጥቀስ፣-
-    የትምህርት ቤቱ ርእሰር መምህር አቶ ታደሰ
-    የትምህርት ቤቱ ገንዘብ ያዥ አቶ ዘለካ።
-    የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አቻም-የለህ እንደሆኑና በቀን አበል ስም ካጠፋፉት ገንዘብ በተጨማሪም የትምህርት ቤቱ ባህርዛፍ ያለህጋዊ ደረሰኝ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወረዳዋ ትናንሽና አንስተኛና ኢንተርፕራይዝ ሃላፊ አቶ አስረስ ለቀን አበል አስመስሎ ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅሙ ያዋለው 22 ሺ ብር የሂሳብ ቁጥጥር ተደርጎ እንደተረጋገጠ በወረዳው ውስጥ በተደረገው ግምገማ ላይ ቢቀርብም እስካሁን ድረስ ግን በባለስልጣኑ ላይ የተወሰደ እርምጃ እንደሌለ ከቦታው የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል።