Monday, April 7, 2014

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ከመጋቢት 12/2006 ዓ/ም ጀምሮ በህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ላይ ተቃወሞ በማካሄድ ላይ እንዳሉ ተገለፀ።



የተቃውሞው መነሻ “በትምህርት ቤቱ በቂ የመማሪያ ማቴሪያል የለም፥ ከተማርነው ውጭ ፈተና እያመጣችሁ እንድንወድቅ እያደረጋችሁን ነው”የሚል ሲሆን በተመሳሳይ ከ5 ሺህ ተማሪዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ከ50 በላይ ነጥብ ስላላመጣችሁ አላለፋችሁም ወድቃችኋል በመባላቸው ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ እየተገደዱ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
     እነዚህ ተማሪዎች በተቃውሞአቸው ከ50 በላይ ነጥብ አምጥተን እያለን ሆነ ብላችሁ በተንኮል እንድንወድቅ ስለፈለጋችሁ ያደረጋችሁት ነው በማለት የጀመሩትን ተቃውሞ አጠናክረው የቀጠሉበት ሲሆን ይህንን ለማረጋጋት ከክልል የመጣው የስርዓቱ ተላላኪ “ደህና ችግር የለም ይሰተካከላል !”በሚል ቃል ገብቶ ለማታለል የሞከረ ቢሆንም እንኳን ተማሪዎች ግን “ህግ የለም”እያሉ  ተቃውሞአቸውን ለተከታታይ ቀናት እንዳሰሙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።