Monday, April 7, 2014

በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽራሮ ከተማ በ1999 ዓ/ም የተጀመረው የኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታ ከመጀመር ውጭ እስካሁን የተሰራ ነገር እንደሌለ ታውቋል።



በመረጃው መሰረት ለኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታ ተብሎ ከፍተኛ በጀት ቢወጣለትም ገንዘቡ በስራው አስተባባሪዎች እንደተጠፋፋና ለህንፃው መስሪያ ተብሎ የተመረተው ብሎኬትም የግንባታ ሰራተኞች እና አሰሪዎች በሌሊት እየሰረቁ ወደ አዲ ሃገራይና ሌሎች በአካባቢው የሚገኙ ከተሞች በመውሰድ እየሸጡት መሆናቸው  ለማወቅ ተችሏል ።
    እየሸጡ ከሚገኙ ሰዎች መካከል አቶ ይርጋ ሃብቱ’ና ለጊዜው ስሙ ያልተጠቀሰ በማዘጋጃ ቤት የሚሰራ ምክትል መሃንዲስና ሌሎች በመተባበር ለመስሪያ ተብሎ ከህዝብ የተዋጣ ጥሬ ገንዘብ’ና ማቴሪያል ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን ጨምሮ አስረድቷል።