ይህ በአካባቢው ለሚሰራው
ግድብ ተብሎ የተመደው ባጀት የወረዳው የውሃና መአድን ሃላፊ የሆነው አቶ ፍሰሃ ኪዳኑ የተባለው ባለ ስልጣንና ሌሎች በገንዘቡ ማጠፋፋት
ተግባር ላይ የተሰማሩ ግብረአበሮቹ ከ 280 ሺ በር በላይ ለጥቅማቸው እንዳዋሉት ለማወቅ ተችለዋል።
መረጃው በማስከተል ለግድቡ መስርያ ተብሎ በየግዜው ሲገዙ የቆዩ በርከት
ያሉ ንብረቶች ከላይ የተጠቀሰው ባለስልጣንና ተባባሪዎቹ በሌሊት ጨለማን ተገን አድርገው በመሸጥ በርከት ያለ የህዝብና የሃገር ገንዘብ
እንዳጠፋፉ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።