Wednesday, April 23, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ የስርአቱ የ24ተኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች ሚያዚያ 1/2006 ዓ.ም ስብሰባ እያካሄዱ በነበሩበት ግዜ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመስማማት እርስ በርሳቸው ሊገዳደሉ እንደቻሉ ታወቀ።



ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት ባእኸር ከተማ በሚገኙ የክፍለጦሩ የመካናዛይድ አባላት በተደረገው ስብሰባ ላይ በተፈጠረው ረብሻና ግርግር ምክንያት አንድ ለግዜው  ያልታወቀ የወታደር አባል ሻምበል ካሳሁን ደመላሽን በጥይት ተኩሶ እንደገደለው ሊታወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮም በወያኔ ኢህአዲግ ወታደሮች መካከል ያለው የብሄር ልዩነት የፈጠረው አለመስማማት እርስ በርሳቸው በአይነ ቁራኛ እየተያዩ እንደሚገኙና በተላይ በተራው ወታደርና በመኮነኖች  መካከል ሰፊ የሆነ ክፍተት ተፈጥሮ በማያቋርጥ ግርግር ውስጥ ተዘፍቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችልዋል።