መረጃው እንደገለፀው በስኳር ፋብሪካው ፕሮጀክት
ለሚሰሩ ሰራተኞች የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ምክትልና የገጠር ልማት ሃላፊ የሆነው ኪሮስ ቢተው ባደረገላቸው ስብሰባ ሰራትኞቹ
በስርአቱ ያላቸው ቅሬታና ጥላቻ እንደገለፁና በተለይ በሁሉም የሃላፊነት ደረጃ ያሉት አስተዳዳሪዎች ሙስና እንደ ዋነኛ መሳሪያ አድርገው
እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ አጋለጡ።
ሰራተኞቹ አክለው’’ ካንተ ጀምሮ እስከ ታችኛዎቹ አስተዳደሮች በሙስና
ተዘፍቃችኃል ሲሉ በመግለፃቸው የተናደደው ኪሮስ ቢተው ይህ የወረኞች
ንግግር ነው ቢኖርም የሚያስገርም አይደለም ዝም ብላችሁ ስራችሁን ስሩ ‘’ ሲል እንደመልሰላቸው ሊታወቅ ተችሏል።
በመጨረሻም በአስተዳዳሪው የተሰጠ የውሸት መልስ ያስቆጣቸው የፋብሪካው
ሰራተኞች በፊናቸው በሙስና መዘፈቅ ወንጀል አይደለም ነው ምትሉን? ሲሉ እንደተናገሯቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።