Wednesday, April 23, 2014

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ኣከባቢ መጋቢት 8, 2006 ዓ.ም ሌሊት ላይ 2 የወያኔ ኢህአዴግ የፖሊስ አባላት ተገድለው እንደተገኙ ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት ኮንስታብል ዘነቡ አለማየሁና መኳንንት በርሄ የተባሉ ሁለት የስርዓቱ የፖሊስ አባላት በጎንደር ከተማ መግቢያ በር ላይ ባልታወቀ ነገር ተገድለው በመገኘታቸው የተነሳ በዚህ የተደናገጡ የስርዓቱ የፖሊስ አባላት በጎንደር ከተማ ህዝብ ነዋሪ ‘ላይ ተገቢ ያልሆነና ፍትህ የጎደለው ድርጊት እየፈፀሙ እንደሚገኙ ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አመለከተ።
    የጎንደር ከተማ ነዋሪ ህዝብ የስርዓቱ አለቅላቂ የሆኑ የፖሊስ አባላትና አስተዳዳሪዎች እየፈፀሙት ካለው አስነዋሪና ስብዕና የጎደለው አካሄድ ካልተቆጠቡ ውልው አድረው የእጃቸውን ማግኘታቸው አይቀሬ ነው እያሉ በሰፊው እየተነጋገሩበት እንዳሉ በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችልዋል።