Sunday, April 13, 2014

የትግራይ ክልል ፀረ ሙስና ሃላፊ ለሆነው ለአቶ ብርሃነ አሰፋ ገንዘብ ያጠፋፉት ሰዎች ኦዲተሮች አጣርተው ክስ አቅርበውለት እያለ ለአራት አመታት ያክል ደብቆት እንደቆየ መጋቢት 24 / 2006 ዓ\ም በተካየደው በክልሉ የካብኔዎች ስብሰባ ላይ ተገለፀ።



እነዚህ ጉዳያቸው በኦዲተሮች ተጣርቶ በሙስና እንደተጨማለቁ ተረጋግጦ ከአራት አመታት በፊት በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች
1.  አቶ ግርማይ ወሉ በሸራሮ የእርሻ ዋስትና ምግብና ሴፍትኔት ሃላፊ
2.  አቶ ፋሲል ኑጉሰ በታሕታይ አድያቦ የዓዲ ፀፀር የእርሻ ሃላፊ
3.  ዋና ኢንስፔክተር ካህሳይ ተጠምቀ በታህታይ ዓድያቦ ወረዳ የፖሊስ የወንጀል ማጣራት ሃላፊ እና ሌሎች ለጊዜው ስማቸው ያልተጠቀሱ እንደሆኑ ተገለፀ፣
     የትግራይ ክልል ፀረ ሙስና ሃላፊው ብርሃነ አስፋ ከተከሳሾች ገንዘብ መቀበሉንና በሙስናው ውስጥ እጁ ስለነበረበት  ወንጀሎኞቹን ወደ ህግ ሳያቀርባቸው ለአራት አመታት ያክል ክሱን ደብቆት እንደቆየ መረጃው አስታውቀዋል።
    በካብኔው ስብሰባ ለምን ደበቅከው ተብሎ ሲጠየቅ ተረስቶ ነው የሚል ከሃቅ የራቀ ምክንያት ባቀረበበት ግዜ ጉዳዩ አሁንም አንዳች ውሳኔ እንዳልተደረገበት መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።