Sunday, April 13, 2014

በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተከስተው ብጥብጥ ምክንያት ከ400 በላይ የሰራዊቱ አባላት በዓዲ ኮኸብ ታስረው እንደሚገኙ ከማእከላይ ዕዝ ሸልኮ የወጣ መረጃ አስታወቀ ።



በመረጃው መሰረት በቅርብ ግዜ በማእከላይ ዕዝ የበታች አዛዦች’ና በግንባሩ አባላት ውስጥ ሃይለኛ የሆነ ብጥብጥ ተከስቶ እንዳለ የገለፀው መረጃው በዋነኝነት የብጥብጡ መነሻ ወደ ዳርፉር ለሰላም ማስከበር ተብሎ በየጊዜው የሚደረገው ምልመላ ትክክል አይደለም ቡዙ አመታት ያገለገልን እያለን በወገንተኝነት የሚገቡትን ቅድሚያ እድል ተሰጣቸው የሚሉ’ና ሌሎችም ማህበራዊ ችግሮች የሚመለከቱ አቤቱታዎች ስለማይመለሱ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
   
    ይህ በህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ደ.ግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት አጋጥሞ ያለው ያለመግባባት በተለይም በግንባሩ የሚገኙ የ33ኛና 22 ክፍለሰራዊት የበላይ ሽማምንት የከፉ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ቀናት ያካሄዱት ግምገማ በትጥቅ ክፍል ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ የኦርዲናንስ ሰራተኞችና በርከት ያሉ መኮንኖች እንዲሁም የበታች አባላት ታስረው እንዳሉ ከዕዙ ሾልከው የደረሱን መረጃዎች አክለው አስታውቀዋል።
    በማነሳሳት ተግባር ከተፈረጁና ታስረው ካሉት 400 የሰራዊቱ አባላት ውስጥ ለመጥቀስ ያክል-
1.    ሻምበል በየነ ለገሰ ከ22ኛ ክፍለጦር
2.    ሻምበል ስንታዮህ አለማዮሁ
3.    ሻምበል ገብረስላሴ ምስግና’ና
4.    ምክትል መቶአለቃ ወለገብሪኤል ስራፋኤል የተባሉት የ33ኛ ክፍለጦር አባላት የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።