Wednesday, April 23, 2014

በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ህሙማን ጭና ወደ ዓዲ ኮከብ ስትጓዝ የነበረች የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በመገልበጥዋ ተሳፍረው በነበሩ ከ25 በላይ የስርአቱ ወታደሮች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገለፀ።




የ33ኛ ክፍለ-ጦር ኦራል ዓይነቷ ወታደራዊ መኪና በሽተኞችን ይዛ ወደ ዓዲ ኮከብ ትጓዝ በነበረችበት ጊዜ በአጋጠማት የመገልበጥ አደጋ በውስጧ የነበሩ 8 ወታደሮች ለጊዜው ህይወታቸው ሲያልፍ 4ቱ ከባድ 13ቱ ደግሞ መካከለኛና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መረጃው አስረድቷል።
    ከመቱት የትወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል- ሻምበል ገብረሂዎት የማሃንዲስ ኣባል፥ ሻለቃ አፅባሃ /ሃዊ አፉ/፥ የሃምሳ አለቃ ይርጋ ካህሳይ፥ ወታደር ደሳለኝ በይሳና ሌሎች መሆናቸውን የገለጸው መረጃው የወያኔ ስርዓት መሪዎች ግን ይህን በቸልተኝነት በሰራዊቱ አባላት ላይ የደረሰ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ ትኩረት እንዳልሰጡት ከሰራዊቱ ውስጥ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ ገለፀ።