Wednesday, April 23, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች መሬት ሸንሻኞችን አስመልክቶ ከአካባቢው አስተዳደር የወረደውን አዲስ መመሪያ እንደተቃወሙት ምንጮች ከቦታው አስታወቁ።



ይህ መጋቢት 28/2006ዓ/ም ከዞን አስተዳደር የእርሻ መሬት መሸንሸንን   አስመልክቶ የወረደውን አዲስ መመሪያ የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች እንደተቃወሙትና የመመሪያው ዝርዝር ነጥቦችም 10 ሄክታር የእርሻ መሬት የነበረው አርሶ አደር ወደ 5 ሄክታር ዝቅ እንዲል፤ የአካባቢው ተወላጅ ለሆነ 5 ሄክታር እንዲሰጥና ከሌላ አካባቢ ለመጣ ደግሞ 2 ሄክታር ይረከብ የሚል ሲሆን ይህ ጉዳይም “በዜጎች መካከል ልዩነት የሚፈጥር ስለሆነ አንቀበለውም” በማለት በአንድ ድምፅ እንደተቃወሙ ለማወቅ ተችለዋል።
   ለዚህ ህጋዊ ያልሆነ አስራር መፍትሄ እንዲደረግለት በነዋሪዎች የተመረጡ ተወካዮች ወደ መቀሌ ከተማ በመሄድ አቤቱታ ያቀረቡት ሲሆን የክልል አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው መጣራት አለባቸው በማለት ተወካዮችን ማለትም አቶ ግርማይ ተክሊት፥ አቶ ተስፋይ አለባቸው፥ ዲያቆን ካህሳይ በርሃነ፥ አቶ ብርሃነ ተስፋኬኤል የተባሉ የህዝብ ጥያቄ የያዙ ዜጎች ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል።