Thursday, April 17, 2014

የላዕላይ አድያቦ ወረዳ አስተዳዳሪዎች የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለጹ።



የላዕላይ አድያቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ልዑል አበራ የተባለው የስርዓቱ ካድሬ በወረዳዋ ለሚገኙ ገበሬዎች ማሰልጠኛ ተብሎ ከሃገርና ከህዝብ ሃብት የተሰበሰበውን ከ600ሺ ብር በላይ ገንዘብ የፋይናንስ ፅሕፈት ቤት ሓላፊው ከገንዘብ ያዡ ጋር በመሆን ይህንን በርከት ያለ ገንዘብ  ለግል ጥቅማቸው እንዳደረጉት ለማወቅ ተችልዋል።
      በመረጃው መሰረት ሁለቱም የስርኣቱ ባለስልጣናት ያላቸውን የስራ ሃላፍነት በመጠቀም ተሻርከው ለስራ ማስፈጸሚያ ተብሎ በወረዳዋ ኮሚቴ የተመደበው ባጀት  በስራ ላይ እንደዋለ አስመስለው ሙሉ በሙሉ ተከፋፍለው እንዳጠፋፉት ያውቅ የነበረ ፍስሃ ገብረሃንስ የተባለ የስራ ባልደረባቸው በወረዳ ደረጃ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ማጋለጥ እንደቻለ ሊታወቅ ተችለዋል።
        ይህ ዜጋ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከሃገር’ና ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ እኒህ ሁለት ባለስልጣናት ተከፋፍለው እንደበሉት  በሚያጋልጥበት ግዜ ላቀረበው ግልጽ ሃሳብ የሚደግፈው አካል ባለማግኘቱ የተነሳ በራሱ ተነሳሽነት መጋቢት 24 2006 ዓ/ም ወደ ሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ በነዚያ የህዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ባዋሉት ባለስልጣናት ላይ ክስ ቢመሰርትባቸውም ተቀባይነት ማግኘት ባለመቻሉ  እስከ ፌዴራል መንግስት ድረስ ሂዶ አብዮቱታውን ማሰማት እንደሚፈልግ ቢናገርም እንኳ በስርአቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ባለው ሙሱናና አድልዎ ምክንያት የሚሰማው ባለስልጣን ማግኘት እንደማይችል በህዝቡ ዘንድ  መነጋገርያ አጀንዳ ሁኖ  እንዳለ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል።