Thursday, April 17, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ነዋሪና በስርአቱ ባለስልጣኖች መሀል እየተካሄደ ባለው የእርሻ መሬት ክፍፍል ምክንያት ትልቅ ችግር እንደተፈጠረ ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



    የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች ወደ ዞኑ በመሄድ ነዋሪውን ህዝብ በመሰብሰብ 8 ወይም 10 ቤተሰብ ያለው አባወራ ምንም ቤተሰብ ከሌለው እኩል 5 ሄክታር የእርሻ መሬት ይሰጠዋል የሚል አዲስ መመርያ ማውረዳቸውን ህዝቡን እንዳልተቀበለውና ስብሰባውን ረግጦት እንደወጣ ለማወቅ ተችለዋል።
    አዲሱን መመርያ ይዞ ወደ መሰብሰብያው አዳራሽ የገባው የትግራይ ክልል ምክትል ኣስተዳዳሪና የገጠር ልማት ሃላፊው ኪሮስ ቢተው የተሰጠውን ተልእኮ ተግባር ላይ ለማዋል በማሰብ ሰአታት የፈጀ ቅስቀሳ ቢያደርግም። ከተሰብሳቢው ለተነሳው ጥያቄና አስተያየት ተገቢ መልስ መስጠት ባለመቻሉ ምክንያት ህዝቡ በአንድ ድምፅ “ፍትሃዊነት የሌለው አሰራር ነው” በማለት በወቅቱ የተዘጋጀውን መድረክ ረግጦት እንደተበተነ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።