በመረጃው መሰረት የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎች
ለወደዱት ወይም ጉቦ ለሰጣቸው ግለ-ሰብ እንደፈለገው መሬት ሲሰጡት ላልወደዱት ወይም ጉቦ ላልሰጣቸው ደግሞ ነጥቀው ለሌላ በማደል
ሆን ብለው ህዝቡ እርስ በራሱ እንዲጋጭ መላ እየፈጠሩ መሆናቸውና በዚህም ምክንያት በወልቃይት ወረዳ አዲ ረመፅ አካባቢ ከሚገኘው
ህብረተሰብ ውስጥ 3 ሰወች በስለት ተወግተው እንደተገደሉ ድርጊቱን የተከታተሉት የአይን እማኞች ገለፁ።
መረጃው በማስከተል
አስተዳዳሪዎቹ በፈጠሩት ፍትሃዊነት ባልነበረው የመሬት ሽንሸናና በተፈጠረው ግርግር ምክንያት ሚያዝያ 6 /2006 ዓ/ም የአቶ ኩራተይ
አስራት መሬት ለመንጠቅ የመጣው አቶ ሙላቴ የተባለው ግለሰብ በስለት ተወግቶ መገደሉን የገለጸው መረጃው የአቶ ሙላቴ ቤተሰብም በአቶ
ኩራተይ ላይ የበቀል ግድያ እንደፈፀሙ በመጥቀስ ባጠቃላይ የ3 ሰዎች ሂወት እንደጠፋ ለማወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይ መንገድ ከዞኑ ሳንወጣ በአዲ ጎሹ አካባቢ በሚገኙ የደን ጥበቃ
ሰራተኞችና ከብት አርቢዎች መካከል የጥይት ተኩስ ልውውጥ መደረጉንና በዚህም ምክንያት ባካባቢው ትልቅ ያለመረጋጋት ሰፍኖ እንደሚገኝ
መረጃው አክሎ አስረድቷል።