በመረጃው መሰረት በ31ኛ ክፍለጦር የስለያ ሃላፊ የሆነው ሻምበል ካልአዩ ከነ ግብረአበሮቹ
ጋር በማህበር ከሸጡት መሳርያና ጥይት የተገኘ 500 ሺ ብር ባከፋፈሉ ላይ በተፈጠረው አለመግባባት ድርሻውን ሳይሰጡት በመቅረታቸው
ምክንያትና በኃላም በክፍለጠሩ በተደረገው ስብሰባ ላይ ሻምበል ካልአዩ በመሳርያዎች መሸጥ ተግባር ላይ እንደተሰማራ በመገምገሙ ምክንያት
ክስብሰባው እንደወጣ በራሱ እጅ ሂወቱን ማጥፋቱን ለማወቅ ተችለዋል።
በክፍለጦሩ ውስጥ እያጋጠመ ላለው ችግር
እንዲፈታ ተብሎ የእዙ ባለ ስልጣን ሜ/ጄነራል ዮውሃንስ ወልደጀወርግስ ወደ ቦታው ደርሶ ሁኔታውን በማስመልከት ስብሰባ ቢያካሂድም
በሰራዊቱ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንዳልተቻለና ይባሱን የከፋ አለመረጋጋት ሰፍኖ እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ኣስታውቀዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የ 22ኛ
ክፍለ ጦር ኣባል የሆነው አንድ ወታደር በተደጋጋሚ ከአመራሮቹ ይደርስበት በነበረው በደል ተማሮ መቶ አለቃ ደረጀ ካሳየ ለተባለው
መኮነን መጋቢት 28/2006 ዓ/ም ብጥይት ተኩሶ እንደገደለው መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል።