Thursday, April 17, 2014

የዓዲ ጎሹ ከተማ ነዋሪዎች በኢ.ሀ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣኖች ትእዛዝ መኖርያ ቤታቸውን በመፍረሱ ምክንያት በረሃ ላይ ተጥለው ብሶታቸውን እያሰሙ መሆናቸውን ተገለፀ።



በትግራይ ምእራባዊ ዞን ዓዲ ጎሹ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በከተማዋ ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ ከ 90-180 ብር ከፍለው የገዙትን ከ30 በላይ የሆኑ መኖርያ ቤቶች በአስተዳዳሪዎች ቀጥታዊ ትእዛዝ እንዲፈርሱ መደረጉን የገለፀው መረጃው ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች የራሳቸው ቤት መሆኑን የባለቤትነት ማረጋገጫ አቅርበው ካሳና ተለዋጭ መሬት እንዲሰጣቸው ወደሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ቢያቀርቡም በአስተዳዳሪዎች የተሰጣቸው መልስ ግን ለሸጡላቹህ እንጂ እናንተን አናውቃችሁም ብለው ስለ-አባረርዋቸው ህፃናት የሚገኙባቸው በርከት ያሉ የቤተሰብ አባላት በረሃ ላይ ተጥለው ለተለያዩ ችግሮች ሰለባ ሁኖው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አስረድተዋል።
     ከዞኑ ሳንወጣ ትርኳን አካባቢ ልዩ ስሙ ሰግለል በሚባል ቦታ የሚኖሩ ወገኖቻችን በህጋዊ መንገድ ከ 1998 - እስከ 1999 ዓ/ም ውስጥ። 20 በ 80 በተሰጣቸው የመሬት ስፋት ላይ 16 የሚሆኑ ሰዎች የሰሩት መኖርያ ቤት ባካባቢው ባለስልጣናት ትእዛዝ ማፍረስ እንደተጀመረና የማፍረሱ ሂደትም ገና በመቀጠል ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል።
    በተመሳሳይ ዜና በወልቃይት ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ልዩ ቦታ ማይ ሑመር ሲኖሩ የቆዩ አርሶ አደሮች ተለዋጭ መሬት ይሰጣቹሃል ተብለው ከአንድ አመት በፊት ከመኖርያ ቤታቸው የተፈናቀሉ 15 አባወራዎች እስካሁን መሬት ስላልተሰጣቸው በከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ወድቀው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል።