Sunday, April 13, 2014

በትግራይ ክልል ለኮንዶምኒየም መስሪያ ተብሎ የተመደበ በጀት ብስራ አስኪያጆች እየተጠፋፋና የተሰሩ ህንፃዎችም ቢሆኑ ጥራት ስለ ሌላቸው አደጋ እያደረሱ መሆናቸው ተገለፀ።



በአዲግራት ከተማ በኮንደሚኒየም የተሰራ ባለ ሶስት ፎቅ ህንፃ መጋቢት 25 /2006 ዓ/ም በድንገት ፈርሶ ብዙ ሰዎችን እንደጎዳ የጠቀሰው መረጃው የፈረሰበት ምክንያትም ለመስርያ የተመደበውን በጀት የኮንዲሚኒየሙ ስራ አስፈፃሚዎች ከኮንራክቶሮችና ማሃንዲሶች ጋር ሽርክና በመፈጠር ገንዘብ ለማትረፍ ሲሉ ደረጃውን ያልጠበቀ የህንፃ መስርያ ስለ ተጠቀሙ መሆኑን መረጃው አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ በመቐለ ከተማ እንዳማርያም አካባቢ የሚገኙ የኮንደሚኒየም ህንፃዎች ስራ ከተጀመረ 6 ዓመታት ማስቆጠራቸውና መጀመርያ ላይ በቂ በጀት የተመድበለት ቢሆንም ስራ ኣስፈፃሚዎቹ የወጣውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ስለ አዋሉት ገንዘብ አልቆብናል በማለት ግንባታውን አቁመው ሌላ በጀት እየጠበቁ እንደሚገኙ ተገልፀዋል።
     ለኮንደምኒየም መገንቢያ እየተባለ በየአመቱ የሚመደበው ባጀት የትግራይ ክልል የኮንደሚኒየም ግንባታ ሓላፊ ኣቶ መኮነን ወ/ስላሴ ከስራ ባልደርቦቹ ጋር እየተመሳጠረ ባጀቱን እያጠፋፋው መሆኑን መረጃው አክሎ  አስረድተዋል።