Sunday, April 13, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ የሚኖሩ ህብረተሰብ በህጋዊ መንገድ የተረከቡትን መሬት በስርአቱ ካድሬዎች እየተቀሙ ለሃብታሞች በመታደሉ ምክንያት ተቃውሞ ማስነሳቱ ተገለፀ።



ይህ በመጋቢት 22 2006 ዓ/ም የተጀመረው ሃይለኛ ህዝባዊ ተቃውሞ መነሻው የስርዓቱ ተላላኪ የሆኑ አስተዳዳሪዎች ብህጋዊ መንገድ ለነዋሪዎች የታደለውን የእርሻ መሬት በመቀማት ለባለ-ሃብቶች እየሸጡላቸው መሆኑ ከቦታው የደረሰን መረጃ አስረድተዋል።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ መሬታቸውን እየተቀሙ ያሉ ወገኖች ለአመታት ግብር የከፈልንበት መሬታችንን ከኛ ቀምታችሁ ለምን ለባለሃብቶች ታድላላችሁ የሚል ጥያቄ ለመሬት ሸንሻኞች እዳቀረቡላቸውና በዚሁ  ጥያቄ ስጋት ላይ የወደቁ አሰተዳዳሪዎችም ለመሬት ሸንሻኞቹ እስከ 40ሺ ብር የሚደርስ ጉቦ ሰጥተው እንዳይናገሩ ስላደረግዋቸው ይህንን የሰማው ህብረተሰብ በበኩሉ መፍትሄ ለማግኘት ሲል ለኣቶ ገ/ሃንስ፥ ለአቶ ይርሳው ይደግና ለአቶ ገ/ስላሴ ፀጋይ የተባሉ ዜጎችን በመወከል እስከ ክልል አቤቱታ አቅርቦው አድማጭ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችለዋል።