Friday, May 23, 2014

የኢትዮጵያና የሱዳንን ድንበር ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከማይካድራና ከበረከት ተመልምለው የተላኩ የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ኮሚቴ አባላቶች ይህ ጉዳይ የሃገር ጉዳይ ስለሆነ አንፈርምም ከአቅማችን በላይ ነው እንዳሉ ከቦታው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



እነዚህ ከማይካድራና ከበረከት ተወጣጥተው ወደ የኢትዮ-ሱዳንን ድንበር ለማዋሰን የተላኩ የኮሚቴ አባላት በህዝብ ሊፈጠር የሚችለው ጥላቻ ስለአሰጋቸው ይህ የሃገር ድንበርን ያህል ትልቅ ጉዳይ የመፈረም አቅም የለንም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ የሰጉ የመንግስት አካላት ደግሞ እንዲፈርሙ እያስገደዱዋቸው ቢሆንም እንኳን እስከ አሁን ድረስ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገልጿል።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የሃገርንና የህዝብን  ክብር  ወደ ጎን በመተው ለግል ጥቅምና ዝና የሚሯሯጡ የህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ሰፊ የሃገሪቱን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፈው መስጠታቸውን በተለያዩ  የመገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወቃል።