Thursday, July 24, 2014

በትግራይ ምእራብ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ልዩ ቦታው “ዓላው” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰኔ 10/2006 ዓ/ም በአካባቢው ሚልሻና በሱዳን ወታደሮች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ፣፣



ምንጭቻችን ከቦታው እንዳስታወቁት በቃፍታ ሁመራ ወረዳ ልዩ ቦታ ዓላው በተባለው አካባቢ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት እየተከተለው ባለው የተሳሳተ መሬት ፖሊስና የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ የመስጠት ሁኔታ በካባቢው ሚሊሻና በሱዳን ወታደሮች ግጭት መፈጠሩና እስካሁንም ብጥብጡ መረጋጋት እንዳላሳየ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
     መረጃው ጨምሮ እንደገለጸው በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በካባቢው መኪና ይዞ ሲያልፍ የነበረው ሙሉ ግደይ የተባለ ኢንቨስተር ከሱዳን ወታደሮች በተተኮሰ ጥይት እንደተገደለ ያሳወቀው መረጃው ከሱ ጋር የነበሩት ሁለት ሰዎችም በከባድ መቁሰላቸውና በተተኮሰው ጥይትም ትራክተርዋ እንደተመታች መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣