Wednesday, July 30, 2014

በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ወረዳ ግልማጫ ቀበሌ ለመብራት መዘርጊያ ተብሎ ከህዝብ የወጣ ከ285ሽህ ብር በላይ ገንዘብ የስርዓቱ አስተዳዳሪዎች እንደበሉት ለማወቅ ተችሏል፣፣



   የወረዳዋ ባለስልጣናት መንግስት መብራት ሊያስገባላችሁ ስላሰበ እያንዳንዱ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ገንዘብ ማዋጣት አለበት ብለው ባወረዱት መመሪያ መሰረት የአካባቢው ማህበረሰብ ከ285ሽህ ብር በላይ ገንዘብ እንዳዋጣና የተዋጣው ገንዘብ ከሁለት አመት በፊት የወረዳዋ አስተዳዳሪ ቢረከበውም ከህዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ ግን ለታሰበለት አላማ ሳይውል እንደጠፋና የኤሌክትሪክ መስመርም እስካሁን እንዳልተዘረጋላቸው ነሪዎችን መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
   የወረዳዋ አብዛኛው ማህበርሰብ በደኢህዴን ኢህአዴግ ስርዓት አስተዳደራዊ አገልግሎት ስለ አልረካ  ስርዓቱን ከሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል ሁነው በሚንቀሳቀሱንና በሚተባበሩ ሰዎች ለሚያነሱት ጥያቄ በአካባቢው ባለስልጣናት ምላሽ እንደማያገኙና ተረግጠው ዝም እንዲሉ እየተደረጉ እንዳሉ በመጥቀስ የስርዓቱ ባለስልጣናት ግን ለማህበረሰቡ አሁንም መብራት እንዲገባላችሁና ለመሰረተ ልማት አግልግሎት ተጠቃሚ እንድትሆኑ ከፈለጋችሁ መጀመርያ የደኢህዴን ኢህአዴግ አባል መሆን የጠበቅባችኋል ስላሉዋቸው ከዚህ በፊት ከልጆቻቸው አፍ ቀምተው ለአካባቢያቸው መሰረት ልማት እንዲሟላላቸው ብለው ያዋጡት ገንዘብም በአስተዳዳሪዎች ተበልቶ መቅረቱንና ዳግመኛ እንዳይጠይቁም ህብረተሰቡ ለወከላቸው አባላት የስርዓቱ ካድሬዎች አስፈራርተው እንደመለሱዋቸው ሊታወቅ ተችሏል፣፣