Wednesday, July 30, 2014

በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የሚኖር ህዝብ በማህበራት ተደራጅቶና ተጋግዞ እለታዊ ኑሮውን እንዳይመራ በፌደራል ፖሊሶች እየተጎሳቆለ እንዳለ ታወቀ፣፣



    በመረጃው መሰረት የአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በማህበራት ተደራጅቶ እለታዊ ኑሮውን እንዳይመራ የገዢውን ስርአት ታጣቂ ሃይሎች በምግብ ቤቶችንና ሻሂ ቤቶች እየገቡ ተፅእኖዎችን በመፍጠር በሃገሩ ሰርቶ እንዳይኖርና አንገቱን እንዲደፋ ለማድረግ ካላቸው ህልም የተነሳ ህዝቡን በሚሰበሰብበት ግዜ ተቃዉሞ ለማድረግ ስለፈለጋችሁ ነው በሚል ምክንያት በፌደራልና በክልል ፖሊሶች ግፍ እየደረሰባቸው መሆኑን ተገለጸ፣፣
    መረጃው በመስጊዶችንና ምግቤቶችም ቢሆን ፖሊሶች እየገቡ ሰዎች እያንገላቱትና እየበቱኑት እንዳሉ ከገለፀ በኋላ እስከ አሁን ድረስም በአንዋር መስጊድ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎቻችን ታስረው ከሄዱ በኋላ ወዴት እንደገቡ እንደማይታወቅና የማሰሩንናና የማንገላታቱ ሁኔታ አሁንም እየቀጠለ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣