Monday, July 21, 2014

የአማራ ክልል 4ኛ አመት 12ኛ የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ያለመስማማት እንደተበተነ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት ስብሰባው ከሰኔ 30 እስከ ሃምሌ 5/ 2006 ዓ/ም በአማራ ክልል የተካሄደው 4 አመት 12 የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ክልሉ የሰራው አዲስ የምክር ቤት ህንፃ ሳይጨረስ በመመረቁ ምክንያት በምክርቤቱ አባላት መካከል ጭቅጭቅ እንደተነሳ ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ እዳለ የአባይ ተፋሰስ ሃገራት 11 መሆናቸው እየታወቀ አዲሱ የምክር ቤቱ ህንፃ በግቢው ውስጥ በአስሩ ሃገራት ብቻ እንዲጠራ በመደረጉ  “የ11ኛዋ ሃገር ለምን አልተካተተም ለቀጣይ ጥሩ ነገር ለምን አይታሰብም”  በማለት በተነሳ ክርክር የቀረበው የምክርቤቱ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳላገኘኛ ተቃውሞ እንደተነሳበት መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል።