Monday, July 21, 2014

በአዊ ዞን ከኮሶ-በር ወደ ሱርታ፤ ቻግኒና ገምባሃን ከሁለት አመት በፊት ለመብራት ተብለው የተተከሉት የኤለክትሪክ ምሶሶዎች አገልግሎት ሳይሰጡ ወድቀው እየተበላሹ መሆናቸው ምንጮቻችን አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት የከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ ተደርጎለት ሲያበቃ አገልግሎት ሳይሰጥ እየወደቀ ያለው የኤልክትሪክ ምሶሶ አስመልክተው የመብራት ሃይል የምዕራብ ዲስትሪክት ሃላፊ ለሆነው በተወካዮቻቸው አድርገው ብሶታቸው ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙ ታውቋል።
    በተመሳሳይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ከቡሬ ከተማ ወደ ቁጭ፤ ፈዘልና ሰርተከዝን ተሳስሮ የተዘረጋ የኤልክትሪክ ሃይል መስመር ከ3 አመት በፊት ጀምሮ አገልግሎት ሳይሰጥ መቆየቱ በስልጣን ያለው የወያኔ-ኢህአዴግ ስርአት ህዝቡ እንደተጠቀመ አድርጎ በተደጋጋሚ የሚያካሄደው ፕሮፖጋንዳ መሰረት የለውም በማለት ህዝቡ እየተነጋገረበት እንደሆነ ምንጮቻችን ከቦታው አክለው አስረድተዋል።