በመረጃው መሰረት ባለፈው
ዓመት ከተለያዩ ያገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው እስካሁን የስራ እድል ያላገኙ በርከት ያሉ ተማሪዎች በቡድን ሆነው ሻይ ሲጠጡና
አብረው ሲያወሩ የታዘቡት የስርአቱ ባለ ስልጣናት ደህንነትና የፀጥታ አባላት በማሰማራት ሃምሌ 6/2006 ዓ/ም 15 ተማሪዎች እንዲታሰሩ
ማድረጋቸው ተገለጸ።
የኢህአዴግ ስርአት ለዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የስራ እድል ስላልተፈጠረላቸው
ከተቃዋሚ ድርጅቶች ተባብረው እንዳይታገሉና ተደራጅተው ተቃውሞ እንዳያስነሱ በማለት በሰላዮቹ በመጠቀም በሚያደርገው እንቅስቃሴ ጥብቅ
ክትትልና ጥበቃ እየተደረገባቸው እንደሚገኙና የሚንቀሳቀሱበት ቦታና መኖሪያቸውን እየተከታተሉ እያስፈራሯቸውና እያሰሯቸው መሆኑን
መረጃዎች ገልፀዋል።
መቐለ ከተማ ውስጥ ከታሰሩት 15 ተማሪዎች የተወሰኑትን ለመግለፅ አሸናፊ
ከለለ፤ ንጉስ ይብራህ ( ወደ ሸራሮ )፤ መብርሂት ታከለ የተባለች ሴት የምትገኝባቸው እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል።