Friday, July 11, 2014

የአዲ-ዳዕሮ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አጥቶ ጥራቱን ካልጠበቀ የጉድጓድ ውሃ ለመጠጣት እየተገደደ መሆኑን ታወቀ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ የአዲ-ዳዕሮ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በከተማው ንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት በመከሰቱ ምክንያት ለሰአታት ያክል ወደ በረሃ በመጓዝ ጥራቱን ካልጠበቀ ውሃ ከጉድጓድ ለመጠቀም ተገድዶ እንዳለና በውጤቱም ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጠ መሆኑን ከደረሰን መረጃ ለመወቅ ተችለዋል።
    አጋጥሞ ባለው የውሃ ችግር በከተማው ያሉት ምግብ ቤቶች፤ መጠጥ ቤትና ሌሎች የንግድ ቦታዎች ስራዎቻቸውን በተገቢው መንገድ እንዳይሰሩ ትልቅ እንቅፋት ስለሆነባቸውና በዚህ የውሃ እጥረት ምክንያትም ትእግስቱ የተሟጠጠው የከተማዋ ህዝብ ያጋጠመውን ችግር እንዲፈታለት በማለት ወደ ከተማው የውሃ ልማት ፅህፈት ቤት አቤቱታውን ቢያቀርብም ጥያቄውን ሰምቶ መልስ የሚሰጠው የመንግስት አካል ሊያገኝ እንዳልቻለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
    ይህ አይነቱ የመጠጥ ውሃ እጥረት በአዲ-ዳዕሮ ከተማ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የሃገራችን ከተሞችና ገጠሮች እየተከሰተ ያለ እሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ በዜና እወጃችን ስንገልፅ መቆየታችን ይታወሳል።