በመረጃው መሰረት የአካባቢው
አስተዳዳሪዎች ምንም ስልጠና ሳይሰጡ ሚሊሻዎች ሁኑ ብለው መሳሪያ ስለ ሚያስታጥቁ በዳንሻ ከተማ ነዋሪ የሆነው ብርሃነ ክንፈ የተባለ
ግለሰብ ሰኔ 26 /2006 ዓ/ም የታጠቀው መሳሪያ ተባርቆበት ምህረት አለምሸት ለተባለች ባለቤቱን እንደገደላት ታውቋል።
መረጃው አስከትሎም በዳንሻ ከተማና አካባቢው ህዝብ ይህ ስርዓት በመሳሪያ
ጉዳይ እውቀት የሌላቸው ሰዎች ተገቢ ስልጠና ሳይሰጥ እንዲታጠቁ ማድረጉ ትክክል እንዳልሆነና መፍትሄ ካልተወሰደ ደግሞ አደጋዎች
እየጨመሩ እንደሚሄዱና አንድ ሁለት እያሉ ሊጨርሱን ነው ሲሉም በርካታዎቹ ነዋሪዎች ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
በተመሳሳይ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ከተማ ማይ-ጋባ ብርሃኔ አስረስ የተባለ በአስገዳጅ የታጠቀ ሚሊሻ መሳሪያው ተባርቆበት ወ/ሮ
መሰረት አጥናፉ የተባለች ባለቤቱን እንደገደላት ቀደም ሲል በዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወሳል።