Sunday, July 6, 2014

በትግራይና በአፋር ክልሎች መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ግጭት የስርአቱ አስተዳዳሪዎች መፍትሄ ማድረግ ባለመቻላቸው ምክንያት ጉዳዩ በከፋ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ።



በአፋር ክልል፤ በበራህሌ ወረዳ፤ የኬናማ ቀበሌ ነዋሪዎች ትግራይ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የአፅቢ ወረዳ እሶት ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን የገለፀው መረጃው አንደኛው ወገን በሌለኛው ወገን በሚያደርሰው ጉዳት ሳብያ ብዛት ያላቸው የቤት እንስሳትና ንብረቶች እንደተዘረፉና አሁንም ሁኔታው እየቀጠለ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
     መረጃው በማስከተል የእሶት ቀበሌ ነዋሪዎች ወደ ኬናማ ጣብያ በመሄድ በበረት ውስጥ የነበሩትን 8 ከብት በእሳት ሲያቃጥልዋቸው ለተቀሩት 18 ደግሞ ዘርፈው የወሰድዋቸው ሲሆን የኬናማ ቀበሌ ነዋሪዎችም ወደ እሶት ቀበሌ በመሄድ ተመሳሳይ ጉዳት ማድረሳቸውን ታውቋል።
     ይህ በትግራይና በአፋር ክልል ነዋሪዎች እየተካሄደ ያለው ጭካኔ የተሞላበት የመጠቃቃት እርምጃ ረጅም ግዜ ያስቆጠረ ቢሆንም የክልሎቹ አስተዳዳሪዎች ላጋጠመው ችግር መፍትሄ እናደርግለታለን በማለት ያገር ሽማግሌዎችንና አንዳንድ ባለስልጣናት የተካፈሉበት ለማስመሰል ብለው ያካሄዱት ስብሰባ ውጤት ማምጣት እንዳልቻለና የተፈጠረውም ጥላቻ የመንግስት እጅ ሳይኖርበት አይቀርም የሚል ጥርጣሬ አሳድሮ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድተዋል ።