Friday, July 11, 2014

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ተማሪዎች ገዥው መንግስት ወጣቶችን ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች እንዲሄዱ ቅስቀሳ ትሰጣላችሁ በሚል ምክንያት እየታሰሩ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



በምንጮቻችን መሰረት በአዲስ አበባ ዩነቨርስቲ ከሚገኙ ተማሪዎች ለወጣቶች ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች እንዲሰለፉ ቅስቀሳ ታደርጋላችሁ፤ በተላይ ደግሞ ከመድረክ ፓርቲ ጋር ሁነው እንዲታገሉን ታደርጋላችሁ በሚል ታማኝነት በሌለው መንገድ ሰኔ 28/2006 ዓ.ም የታሰሩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አቸናፊ መገርሳና ሞገስ ካልአዩ የተባሉ የኢንጅነሪንግ ተማሪዎችና ሌሎችም ስማቸው ያልተጠቀሱ የሚገኙባቸው በርከት ያሉ ተማሪዎች በስርዓቱ መታሰራቸው ታወቀ።
    እነዚህ ፀረ ኢህአዴግ ትቀሰቅሳላችሁ የተባሉ ተማሪዎች በስርዓቱ ታጣቂዎች ተጠልፈው ከተወሰዱ በኋላ እስካሁን የታሰሩበት ቦታ ስላልታወቀ ቤተሰቦቻቸው በከባድ ጭንቀት ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።