Thursday, August 7, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሸራሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የፖሊስ ባለ ስልጣኖች ሃላፊነታቸው ተጠቅመው የህዝብ መሬት እየወረሩ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆናቸውን ተገለፀ፣፣



በሸራሮ ከተማ ፖሊስ ጣብያ ፊት ለፊት የሚገኘው መሬትና መኖርያ ቤቶች መንግስት አቅም ለሌላቸው ድሃ ወገኖች ይሰጣቸዋል እያለ ቢናገርም የከተማው የፖሊስ የበላይ አዛዦች ግን ስልጣናቸውን በመጠቀም መሬቱና መኖርያ ቤቱን ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሆነና ይህን ተግባር እየፈፀሙ ከሚገኙትም ኢንስፔክተር ተስፋይ የተባለ የፖሊስ አዛዥ እንደሆነ መረጃው አስታውቋል፣፣
    ይሀው ግለሰብ ይዞት ባለው ስልጣን ተጠቅሞ የህዝቡን መሬትና መኖርያ ቤት ወደ ግሉ ባማስገባትና ለድሆች በማከራየት የቤትና የመብራት ኪራይ ተቀብሎ ለግሉ እየተጠቀመበት መሆኑን ተገልጸዋል፣፣
    ኪራይ ለመክፈል እየተገደዱ ያሉትን ወገኖች ለግለ ሰቡ መክፈላቸው ትክክል እንዳልሆነና መፍትሄ እንዲደረግላቸው ወደ ሚመለከታቸው አካላት ብሶታቸውን ቢያቀርቡም እንስፔክተሩ ከባለስልጣኖቹ ተመሳጥሮ የሰራው በመሆኑ ያቀረቡትን ጥያቄ ውጤት ሊያገኙለት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
    የፖሊስ አዛዡ ከህዝቡ ሊመጣበት ከሚችለው ተቃውሞ ለመከላከል በማሰብ ሚስቱ ባለፈው የትግል ወቅት ታግላ እንደነበረችና አቅም እንደሌላት በማስመሰል መኖርያ ቤተቹ ወደ ራስዋ ይዞታ አስቀይራ እየተጠቀመችበት ባለችበት ባሁኑ ግዜ ከአግባብ ውጭ በሆነ መንገድ በደል እየደረሰባቸው ያሉ ድሆች ወጎኖቻችን ግን ወደ ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ግዚያቸውን በከንቱ እያሳለፉት እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣