Saturday, August 9, 2014

በአፋር ክልል በራህሌ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች ባካባቢው ማህበረሰቡ ለይ ግፍ በመፈጸማቸው ምክንያት ስሜት ውስጥ ገብቶ የቆየውን ህዝብ በወታደረቹ ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ፣፣



ካካባቢው በተገኘው መረጃ መሰረት በበራህሌ ወረዳ፤ ሳባ በተባለው ቀበሌ የሚገኙ የ 21 ክፍለጦር ወተሃደሮች ሃምሌ 21/2006 ዓ/ም በራህሌ ወረዳ በሚገኘው ሰላማዊ ህዝብ ላይ ግፍ መፈፀም በጀመሩበት ወቅት ህዝቡ የበቀል እርምጃ እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል፣፣
      በደል የደረሰበት ህዝቡ በወታደሮቹ የበቀል እርምጃ በወሰደበት ግዜ የ8 ሻለቃ 2 ሃይል ምክትል አዛዥ የነበረውን መቶ አለቃ ገብሩ የተባለውን በከባድ ተደብድቦ ለህክምና ወደ መቐለ እንደተወሰደ የገለጸው መረጃው ከሲብሉ ማህበረሰብም ዓብደልወሃብ ወይም ወዲ ሻምበል በሚል የሚጠራውን ግለሰብ በወታደሮቹ ክፉኛ ተደብድቦ መቐለ ከተማ ውስጥ በህክምና እንደሚገኘ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣