Thursday, August 14, 2014

የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪዎች ወጣቶች በብዛት ወደትግልና ወደስደት እየጎረፉ በመሆናቸው ምክንያት ለአካባቢው ማህበረሰብ ቀጣይነት ባለው ስብሰባ ጠምደውት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



ምንጮቻችን ከቦታው እንደገለፁት የአሕፍሮም ወረዳ አስተዳዳሪ ሰለሞን ይህደጎ እና የዝባን ጒላ ቀበሌ አስተዳዳሪ አለነ ተስፋማርያም እንዲሁም የቀበሌዋ የፀጥታ ሓላፊው አባዲ ገብረኪዳን የተባሉ የስርዓቱ ካድሬዎች ለዝባን ጒላ ቀበሌ ነዋሪ ህዝብ ጭንቀት በወለደው በማያቋርጥ ሰብሰባ ላይ ጠምደውት እንደሚገኙ ለማወቅ ትችሏል።
     ካድሬዎቹ እያካሄዱት ባለው ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢው ማህበረሰብ።  በብዛት ወደ ትህዴን እየጎረፉ ላሉት ወጣቶች ማቆም ከቻላችሁ አመት ሙሉ ሊያበላችሁ የሚችል ቀለብ እንሰጣችሁአለን በተመሳሳይ ወደ ስደትም ለሚሄዱት ማቆም ከቻላችሁ እንደዚሁ ከመንግስት ድጋፍ ይደረግላችኋል በተረፈ ግን ይህንን ማድረግ ያልቻለ ሰው  ጠንካራ እርምጃ የምንወስድበት መሆናችንን ማወቅ ይገባዋል በማለት ማስፈራራት የተሞላበት ንግግር በስብሰባው ላይ እንዳሰሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስርድተዋል።