Thursday, August 14, 2014

ባለፈው ሳምንት የወያኔን ኢህአዴግ ስርአት የተቃወሙ ወጣቶች ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ተቀላቀሉ።



ወደ ማሰልጠኛው ከተቀላቀሉት ወጣቶች ጥቂቶቹን ለመግለፅ-
1.  ዜናዊ ኪዳነ ተስፋይና ተስፋአለም ታደሰ ገብረሂወት ሁለቱ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን። ሸራሮ ወረዳ ሙሴ ቀበሌ 
2.  ወታደር ሮቤል ገብረመስቀል መለስ። ከምእራብ እዝ 12ክፍለጦር፤ 5 ሬጅመንት፤ ሃይል 5፤ 1 ጋንታ 3 ቲም
3.  ሙለይ ሓድጉ ወልዱ ከማእከላይ ዞን፤ ጣንቋ አበርገለ ወረዳ፤ ሓዱሽ ዓዲ ቀበሌ
4.  አስመላሽ አብርሃለይ ኪዳነ ከምእራባዊ ዞን፤ ሰቲት ሁመራ ወረዳ፤ 02 ቀበሌ
5.  ሃይለ ተሰማ ወለመድህን ክምስራቃዊ ዞን፤ ውቕሮ ክልተውላዕሎ ወረዳ፤ ማይ ዳዕሮ ቀበሌ ሲሆኑ።

 በተለይ ወታደር ሮቤል ገብረመስቀል የኢትዮጵያ ሰራዊት ተጨባጭ ሁኔታ አስመልክቶ ለትህዴን ሬድዮና ቴለቭዥን ፕሮግራም ዝግጅት ክፍል በሰጠው መረጃ እንደገለፀው የስርአቱ ወታደር በየወሩ የሚሰጠውን ደሞዝ አነስተኛ በመሆኑና አጋጥሞ ባለው የዋጋ ንረትና በየወሩ ለተለያዩ ጉዳዮች በሚከፈለው መዋጮ ደሞዙ ስለሚቆራረጥ። በከባድ ችግር ላይ መውደቁንና የ7 አመት አገልግሎት ከጨረሰ ብኋላ በግዜው እንደማይሰናበት፤ በሰራዊቱ ውስጥ የብሄር ልዩነት እንደሚታይ፤ ላመራሮች ሂስ መሰንዘር እንደማይቻልና ከሞከረም የአሸባሪዎች ተባባሪና ፀረ ሰላም ተብሎ እንደሚታሰር አስረድተዋል።
   ወታደር ሮቤል በማስከተል- ራሱም ቢሆን ከአመራሮቹ መስማማት ስላልቻለ በቤንሻንጉል ክልል ዞን በፓዊ ወረዳ ለአንድ አመት ከሰዎስት ወር ያህል መታሰሩን ከገለፀ በኋላ በርካታ መኮንኖች የሚገኙበት የምእራብ እዝ አባላትና በሺዎች የምቆጠሩ ሌሎች ወታደሮች ታስረው እንደሚገኙ ገልፀዋል፣
    ከታሰሩት ከፊሎቹን ለመግለፅ ያህል-
*    ኮለኔል ገብረመድህን ገብረመስቀል
*    ሌ/ኮለኔል እስቲፋኖስ
*    ሻለቃ አብርሃ
*    ሻንበል ግደይ ሓዱሽ
*    መቶ አለቃ መሃመድ ዑመር
*    አምሳ አለቃ ዘሪሁን ሽናሞ
*    አስራ አለቃ ሃፍቶም ገብረስላሴና
*    ወ/ደር ሃፍቴ መንገሻ የሚገኙባቸው በርከት ያሉ ወታደሮች  ተስረው እንደሚገኙ ጨምሮ አስረድተዋል።