Tuesday, September 30, 2014

በሁሉም የትግራይ ዞኖች የሚገኙ የትምህርት ቤት መምህራን በህወሃት ኢህአዴግ ካሬዎች በተደረገላቸው ስብሰባ ላነሷቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ እንዳልተሰጣቸው ተገለፀ።



በመቀሌ በአክሱም ዓዲ ግራትና ሽሬ በአጠቃላይ በሁሉም ዞኖች የሚገኙ መምህራን ከአንድ ሳምንት በላይ የወያኔ ካድሬዎች አስገድደው ስብሰባ ላይ ጠምደዋቸው እንደሰነበቱ የገለፀው መረጃው የስብሰባው አጀንዳም የመንግስት ፖሊሲ፤ የህወሃት ታሪካዊ አመጣጥና ሌሎችንም ያካተቱ መሆኑን የገለፀው መረጃው  ስበባው ላይ የተሳተፉት መምህራን መድርኩ  ለፖለቲካ መነገጃ ሲባል የተደረገ ቅስቀሳ እንደሆነ በመግለፅ ይህም ህሊናችንን ለማደናገር ሆን ተብሎ የተቀነባበረ በመሆኑ አንቀበለውም በማለት ተቃውሞአቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው ጨምሮ መምህራነቹ በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብአዊና  ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት አስመልክተው ያቀረቡትን በርካታ ጥያቄዎች የስብሰባው መሪዎች በአግባቡ ሊመልሱሏው ስላልቻሉ ስብሰባው ያለ-ማጠቃለያ ፍሬ አልባ እንደተበተነ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስታወቀ።