Tuesday, September 30, 2014

አክሱም ከተማ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ውስጥ በሚፈጸመው ብልሹ አሰራር ምክንያት ተገልጋዩ ህዝብ እየተንገላታና ላልተፈለገ ወጪ እየተጋለጠ መሆኑን የደረሰን መረጃ አስታወቀል።



ከቦታው በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን አክሱም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቅድስት ማርያም ሆስፒታል ስርአቱ የሪፈራል ሆስፒታል እንደሆነ ቢገልፀውም ተግባር ላይ ግን በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙት በግል ጥቅም የሚንቀሳቀሱ ዶኩተሮች ለህዝቡ ተብሎ የመጣውን መድሃኒት በተለያየ መንገድ ወደ ግል ክሊኒካቸው እየወሰዱ ከመጠን በላይ በሆነ ገንዘብ መልሰው ለህዝቡ እየሸጡት መሆናቸው ተገለፀ።
    መረጃው ጨምሮ በሆስፒታሉ የሚገኙት እንደ ኤክስረይ የመሳሰሉ ትላልቅ መሳርያዎች እንዲበላሹ ማድረጋቸውንና መሳርያውን ለመጠገን ለመጣ ባለሞያ በድብቅ 9 ሺህ ብር በመስጠት ሳይሰራው እንዲሄድ በማድረግ ታሞ እየተሰቃየ ያለው ህመምተኛ ሳይወድ በግል ክሊኒካቸው ውስጥ እንዲታከምና ከመጠን በላይ የሆነ ገንዘብ እንዲከፍል እያስገደዱት መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።
    ሞያዊ ስነምግባር ባልሆነ መንገድ ችግር እየፈፀሙ ከሚገኙት አንዱ የሆነው ዶኩተር አምሳሉ ቢቶው የተባለ ግለሰብ የህወሃት ኢህአዴግ ስርአት ታማኝ ካድሬ ስለሆነ ብቻ ከደህንነት አባላትና ከጤና ጥበቃ ሃላፊው አቶ ሓጎስ ጎድፋይ ጋር ጥብቅ ግንኝነት በመፍጠር እየፈፀመው ላለው ብልሹ አሰራር የተቃወሙትን ሰራተኞች በሃሰት በመወንጀል ከስራቸው እንዲባረሩና ወደ ሌላ ቦታ እንዲቀየሩ እያደረጋቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው ከቦታቸው እንዲቀየሩ ከተደረጉት ውስጥም ዶ/ር አስማማው ዮሴፍ የተባለው  ሸራሮ ከተማ ውስጥ ተመድቦ እንዲሰራ መደረጉ ተገልፀዋል።