Sunday, October 12, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ ካድራ ከተማ ለስራ ፍለጋ ከአማራ ክልል የመጡ ወገኖቻችን በመካከላቸው በተፈጠረ ግጭት የዜጎች ህይወት እንደጠፋ ምንጮቻችን ገለጹ፣




በመረጃው መሰረት እነዚህ ከአማራ ክልል ለስራ ፍለጋ ወደ ማይ-ካድራ ከተማ የሚሄዱ ወገኖቻችን፤ የወሎና የጎጃም ተወላጆች በሚል በመካከላቸው  አካባቢያውነት የፈጠረው ጎራ የለየው ግጭት መነሳቱና በውጤቱም ስማቸው በወል ያልታወቁ 5 ወገኖቻችን በቢላዋ ተወግተው ህይወታቸው እንዳለፈ ታወቀ፣
    መረጃው አክሎ የወሎና የጎጃም ተወላጆች በመካከል በተፈጠረ ግጭት የሞቱት ዜጎቻችን እስካሁን ገዳዮቻቸው የልተያዙ ሲሆኑ፤ የከተማዋ የጸጥታ አስከባሪዎች ወንጆሎኞችን ለመያዝ ያደርጉት ጥረት ካለመኖሩ የተነሳ፤ ነዋሪዉ ህዝብ ስርአቱ ሆን ብሎ ጠብ እንዲፈጠር አድርጓል በማለት ጥርጣሬያቸውን በመግለጽ ላይ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣