Monday, October 13, 2014

የመቐለ ከተማ ፖሊሶች የደመወዝ ጭማሪ ለሁሉም የመንግስት ፅህፈት ቤቶች ሲጨመር ‘ለምን ለኛ ጭማሪ የማይደረግ በማለት ጥያቄ ማንሳታቸው ተገለፀ፣





እነዚህ በመቐለ ከተማ በቀዳማይ ወያኔ ክፍለ ‘ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ተመድበው የሚሰሩ አባላት፤ የፖሊስ አዛዦች ከአባላት ጋር በመሆን መንግስት በሁሉም የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ የፔሮል ማስተካከል ሲያደርግ በእኛ ላይ ለምን? የደመወዝ ጭማሪ ሊያድርግ ያልቻለው? እንደማነኛውም የሃገራችን የመንግስት ሰራተኛ ለምን አልታየንም? በማለት ጥያቄአቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ፣
  መረጃው ጨምሮ እንደሚያስረዳው ፖሊሶች ኮማንደር አረጋዊ በተባለ አዛዣቸው እየተመሩ እያነሷቸው ካሉ ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ።- “እኛ ለምን እንደሌላው የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ ጭማሪ የማይደረግልን?”፤ “እየተከፈለን ያለው ደመወዝ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ኑሮአችንን ልንመራ አልቻልነም፤ እጅግ ተቸግረናል።” እያሉ ደጋግመው በመጠየቅ ‘ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣