Monday, October 13, 2014

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የሃገር ሃብት እየቀሙ ለግል ኑሮአቸው እያዋሉት መሆናቸውን ተገለፀ፣





እኒህ በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  ባለስልጣናት በሃገር እና በህዝብ ሃብት ከውጭ ሃገራት የተገዙ ማሽኖችን ለባለስልጣናት የግል ጥቅም እየዋለ መሆኑን የገለፀው መረጃው በዚህ የሙስና ተግባር ከተሰማሩት መካከል አንዱ የትግራይ ክልል የትምህርት ቢሮ ሃላፊ የሆነው ጎበዛይ ወልደ አረጋይ መሆኑን ተገልጿል፣
  ይህ ከትግራይ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆነው ጎበዛይ ወልደአረጋይ ከውጭ ሃገራት ተገዝተው የመጡ ጀኔረተሮችንና ሌሎች ንብረቶችን ወደ ተገልጋዩ ህዝብ ሳይደርሱ ለግል ጥቅሙ እያዋለው መሆኑን መረጃው አስረድቷል፣
    የቢሮው ሰራተኞች ታዛቢው ህዝብና ፖሊሶች በዚህ ባለስልጣን እየተፈፀመ ያለውን ሙስና መፍትሄ እንዲሰጥበት ወደ ሚመለከተው አካል ያቀረቡትን አቤቱታ ሃላፊዎች ርስበርሳቸው እየተሻረኩ ሰሚ ጆሮ እንዳሳጡት ለማወቅ ተችሏል፣