Saturday, November 22, 2014

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ልጉዲ አካባቢ በቀን ስራ ላይ በተሰማሩ ዜጎች መካከል በተነሳው ጠብ የሰው ህይወት እየጠፋ እንደሚገኝ ተገለፀ።



     ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ መሰረት እነዚህ የወሎና የጎጃም ተወላጅ የሆኑ በቀን ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች መነሻው ባልታወቀ ምክንያት በመካከላቸው በተነሳው ከባድ ግጭት ለሞትና ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጋልጠው እንዳሉ የገለፀው ይህ መረጃ ይህንን ግጭት ለማረጋጋትም እስካሁን በጉጅሌው ኢህአዴግ ስርዓት ምንም አይነት እርምጃ እንዳልተወሰደ ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
     በአንፃሩ የሱዳን ወታደሮች ወደ አካባቢው በመግባት የተፈጠረውን ግጭት ሊፈቱት መሞከራቸውና ግጭቱ ሆን ተብሎ በገዢው ስርዓት የተፈጠረ እንደሚሆን የአካባቢው ነዋሪዎች በሰፊው እየተነጋገሩበት እንደሆነ መረጃው አመለከተ።
     በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ክልል ማይ ካድራ ከተማ ለቀን ስራ ብለው በሄዱ ወገኖች በስልጣን ላይ የሚገኙት የስርዓቱ ካድሬዎች በቆሰቆሱት ጥላቻ የወሎና የጎጃም ተወላጆች የሚል አካባቢያዊነት የተጠናወተው የማናከስ እኩይ ተግባር  በመካከላቸው በተፈጠረው ግጭት ስማቸው በግልፅ ያልታወቁ 5ት  ወገኖቻችን በቢላዋ ተወግተው ህይወታቸው እንዳለፈ ከዚህ በፊት በዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወሳል።