Friday, January 9, 2015

ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ታህሳስ 14/ ቀን 2007 ዓ.ም በሽረ ከተማ ከተወሰኑ ሃብታሞችና የመንግስት ሰራተኞች ጋር ተገናኝቶ በመሄዱ የተበሳጨው የሽረ ከተማ ነዋሪ ህዝብ በከተማዋ አስተዳደር ለተደረገላቸው ስብሰባ እንደተቃውሙት ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የከተማዋ አስተዳዳሪ ታህሳስ 16/ ቀን 2007 ዓ.ም ለሽረ ከተማ ሰብስቦ ሃይለማርያም ደሳለኝ ያደረገውን ስብሰባ መነሻ በማድረግ መንግስታችን እየሰራ ቆይተዋል አሁንም ይሰራል፤ እያለ የማይተገበር የተለመደ የማታለያ ቃል መናገር በጀመርበት ሰዓት ማህበረሰቡ በበኩሉ ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ ለሽረ ከተማ ማህበረሰብ ግምት ውስጥ ሳያስገባ የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ጠርቶ ስብሰባ ማካሄዱ ትላንት የሽሬ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ታሪክ ሰሪ ጀግና እየተባለ መስዋእትነት የከፈለው ህዝብ ተረስቷል በማለት ይካሄድ የነበረውን ስብሰባ እንደተቃወሙት ለማወቅ ትችሏል።
   የአስተዳድሩን የማይተገበር ቃል ሃሳባቸውን በማቅረብ በግልፅ ከተቃወሙት የሽረ ከተማ ነዋሪዎች ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ተኹሉ ሓጎስና ብርሃነ መኮነን የተባሉ ከቀበሌ 03ና ሌሎችም የሚገኙባቸው እንደሆኑ ምንጮቻችን ከከተማዋ ጨምረው ገልፀዋል።