በአካባቢው የሚገኙ ምጮቻችን እንደገለፁት የሰሮቃ ከተማ ነዋሪዎች ፍትሃዊነት
በጎደለው የመሬት አስተዳደር እየተሰቃዩ ሲሆን የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መለያ የሆነውን ባለኮከብ ባንዲራ በመተው ምንም ምልክት የሌለውን
የሃገራችንን ባንዴራ በመያዝ “ይህ ሰንደቅ አላማ በነበረበት ጊዜ የነበረው መሬታችን ይመለስልን” የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በመያዝ
ገዥው መንግስት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ገልፀዋል።
መረጃው ጨምሮ የሰሮቃ ከተማ የፖሊስ አባላት
ይህንን ባንዴራ ይዛችሁ ሰላማዊ ሰልፍ አትወጡም በማለት ሰልፉን ለማገድ ቢሞክሩም በስርዓቱ የተማረረው ህዝብ ግን ሊታገት እንዳልቻለ
ለማወቅ ተችሏል።
ከአካባቢው ሳንወጣ ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓም አንገረብና ሰሮቃ የሚገኙ
ትላልቅ ወንዞችን በሚያገናኘው የአውደራፊ ድንበር በሆነ ቦታ ላይ የሁለቱ ክልል ልዩ ሃይል ታጣቂዎች በጀመሩት ተኩስ በርካታዎች
መሞታቸውንና ብዙዎቹም መቁሰላቸውና ከሞቱት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህልም ከትግራይ ክልል ተሾመ በለጠ ናስር አብድልቃድር፥ በርሀ
ጋይም የተባሉት ሲሆኑ ከአማራ ክልል ደግሞ ሞራድ አብድልዋስዕ፥ ገብረአምላክ ታደሰ፥ ሙክታር አብድልአሚን፥ አለነና ሌሎችም እንደሚገኙ
የገለፀው መረጃው አሁንም በስፍራው ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ እንደሚገኝ አስረድቷል።