ምንጮቻችን የላኩት መረጃ እንደሚያመለክተው
በሽራሮ ከተማ የሚገኙ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ምርጫ በተቀራረበበት ሰዓት ያሰጉናል ያሏቸውን ንፁሃን ሰዎች ምክንያቶችን
እየፈጠሩ ያለምንም ምክንያት እያሰሯቸው መሆኑን ገልፆ በቅርቡ እንኳን የቱሪስት ሆቴል ባለቤት የሆነውን ብርሃኔ የተባለ ዜጋ በቤቱ
3 ሽጉጥ፥ 197 ሺህ ብርና 51 ኩንታል ዕጣን ተገኝቷል በሚል ውሸት ከልጁ ጋር ያለምንም ፍርድ አስረው እያሰቃዩት መሆኑን ታውቋል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት በምዕራብ፤ በሰሜናዊ ምዕራብና በማዕከላዊ ዞን የሚገኙ ህዝቦችን በትህዴንና በአረና ድርጅቶች
በብዛት ተደራጅተው ስለሚገኙ ይህንን ለመቀየር የሚታሰረውን እያሰርን የሚመከረውን እየመከርን ሰፊ ስራ እንሰራለን የሚል ድምዳሜ
መድረሳቸውንም ለማወቅ ተችሏል።