Friday, March 6, 2015

በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች ከአሁን በፊት ከነበረው በከፋ መልኩ ፀረ ህወሓት-ማሌሊት ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸው ታወቀ።



    ምንጮቻችን እንደገለፁት 40ኛው የካቲት 11 የህወሓትን የልደት በዓል ለማክበርና የድርጅቱ አመራሮች ምርጫ ላይ እንዲያሸንፉ  እያካሄዱት ባለው ሰፊ ቅስቀሳ በሌሎች ክልሎች የሚኖሩትን የትግራይ ተወላጆች  በተለየ ሁኔታ እየሰበሰበ ድርጅታችሁን ህወሓት መደገፍና መምረጥ አለባችሁ፤ ሌሎች ድርጅቶችን ከመረጣችሁ ግን እንደ ቀድሞዎቹ ስርዓቶች እየረገጡ ይገርፏችኋል እያሉ በሚሰብኩበት ጊዜ ህዝቡ ግን ተዋውቀናል ከአሁን በኋላ ግን በትግራይ ተወላጆች የምትነግዱበት ጊዜ የለም በማለት መልስ እየሰጧቸው እንዳሉ ተገለፀ።
   እነዚህ በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች  በህወሓት ባለስልጣናት እየተካሄደ ያለውን በስልጣን እንዲኖሩ በማሰብ አግዙን የማለት ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ህዝቡ በጣም ተሰላችቶ እንዳለ ከገለፀ በኋላ በተለይ ደግሞ በ17ዓመት የትጥቅ ትግል ተሳትፎ የነበረው ተጋይ ከፊታቸው በመቆም ዘላለም በትግራይ ልጆች ትከሻ እያላገጣችሁ ለመኖር አታስቡ ከንግዲህ ይበቃል ስንት ጊዜ እንታለላለን በማለት ተስፋ እያስቆረጣቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።