Thursday, April 30, 2015

በላዕላይ አድያቦ ወረዳ ዓዲ ነብሪኢድ አካባቢ በወታደሮችና በነዋሪው ማህበረሰብ መካከል ከባድ ግጭት እንደተፈጠረ ተገለፀ።



    ባገኘነው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ ነብሪኢድ አካባቢ የሚገኙ  የ31ኛ ክፍለ ጦር አባላት የሆኑ የኢህአዴግ ወታደሮች በአካባቢው ለብዙ አመታት ተከልክሎ በነበረው የደን ቦታ በመግባት የደን ማውደም ተግባር እየፈፀሙ እንደሚገኙና በዚህም ምክንያት ነዋሪው ህብረተሰብ በመቆጣት ከወታደሮቹ ጋር በከባድ ግጭት ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ አመለከተ።
   ይህ በወታደሮቹ የተደፈረው ደን በተለያዩ የቤት እንስሳዎችም ሆነ በሰዎች እንዳይረገጥ እየተባለ በነዋሪው ህብረትሰብ ስምምነት መሰረት ተከልክሎ የቆየ ሲሆን አሁን በአካባቢው የሰፈሩ ወታደሮች ግን የአካባቢውን ህብረተሰብ ህግ በመጣስ ለብዙ አመታት ተጠብቀው የቆዩ የተለያዩ ዛፎችን እየቆረጡ ማውደም በመጀመራቸው ምክንያት መላው የአካባቢው ማህበረሰብ ተግባሩን ስላልተቀበለውና ላነሳው ተቃውሞም የሚሰማው አካል አጥቶ በሃይል ለመፍታት ቢሞክርም ወታደሮቹ ግን ከበፊቱ በባሰ መልኩ መሳሪያቸውን ወድረው ህብረተሰቡን እያስፈራሩ የአካባቢውን ደን እየቆረጡት በመሆናቸው ምክንያት ግጭቱ ገና እየቀጠለ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።