የማኣከላዊ እዝ 23ኛና 33ኛ ክፍለጦር
የሰራዊት አባላት የሆኑት ወታደሮች ሃምሳ አለቃ ዓሊ እንዴሬ፤ ምክትል አስር አለቃ ከበደ አበጀና ወታደር መሳይ፤ የሚገኙባቸው በሃላፊዎቻቸው
እየወረደባቸው ያለውን የአስተዳደር አድልዎና የኑሮ ውድነትን ሊቋቋሙት ባለመቻላቸው ምክንያት ሰራዊታቸውን በመተው እንደጠፉ ምንጮቻችን
ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ የ24ና የ48 ሰአት ፋቃድ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ በሽራሮ ከተማ እንዲገናኙ ተቀጣጥረው አንድ ላይ ሁነው
የጠፉት. 2 ምክትል የአስራ አለቃ፤ 3 የአስራ አለቃ፤ 3 ተራ ወታደሮችና አንድ የአምሳ አለቃ በጠቅላላ 9 የኢህአዴግ መከላከያ
ሰራዊት አባላት ሚያዚያ 14 /2007ዓ/ም ብቻ፣ ክፍላቸውን ትተው እግራቸው ወዳመራቸው እንደጠፉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።