Saturday, May 2, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት በአስተዳዳሪዎችና በስርዓቱ አባላት ግፍ እየተፈፀመባቸው መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



    ምንጮቻችን ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች እንደገለፁት የገዥው ህወሃት/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት አስተዳዳሪዎችና አባላት መምህር  ገብሩ ሳሙኤልና ሌሎችንም የሰማያዊ ፓርቲ የተቃዋሚ ድርጅት አባላቶችን በሚሰሩበትና በተለያዩ ቦታዎች እየተከታተሉ እናንተ አሸባሪና ፀረ ልማት ናችሁ በማለት እያስፈራሯቸው መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
     መረጃው ጨምሮም በአዲስ አበባ ከተማ ሚያዝያ 14/ 2007 ዓ/ም የተደረገውን ሰፊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የገዥው ስርዓት ካድሬዎች አዲ ጎሹ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የተቃዋሚ አባላትን ወደ መኖሪያ ቤታቸውና የስራ ቦታቸው በመሄድ እናንተ አጭበርብራችሁ በህዝብ ተቃውሞ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግን መንግስት ገልብጣችሁ ስልጣን ለመጨበጥ እያሰባችሁ ነው በሚል የማስፈራራት ዘመቻ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።