Saturday, May 23, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 6/ 2007 ዓ/ም መብራት በመጥፋቱ ምክንያት ስራ ጀመረ የተባለው የባቡር መንገድ እንዳቆመ ለማወቅ ተችሏል።



  በከተማው የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት በአዲስ አበባ ከተማ ጎተራና ሲ.ኤም.ሲ  አካባቢ የሚገኝ የመብራት ሃይል መስመር ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ/ም ሌሊት ጀምሮ ጠቅልሎ ስለተቋረጠ በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ ፈስሶበት የተሰራ የባቡር መንገድ ስራ እንደጀመረ በገዥው ስርዓት በተለያዩ መድረኮችና ሚዲያዎች ከተነገረለት በኋላ ምንም አገልግሎት ሳይሰጥ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስራ ማቆም መጀመሩ ለከተማዋ ህዝብ መነጋገሪያ ርዕስ መሆኑ ታውቋል።
     በመጓጓዣ እጥረት ከስራው እየተሰናከለ የሚገኘው ህዝብ ፖለቲካዊ ኪሳራ እንዳያጋጠመው ስጋት ላይ የወደቀ አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት ወደ አካባቢው ታማኝ ካድሬዎችን በማሰማራት ተቃዋሚ ድርጅቶች ሆን ብለው ህዝቡን ከመንግስት ጋር ለማጣላት የኤሌክትሪክ መስመር ቆርጠውት አደሩ በማለት ቅስቀሳ በመጀመሩበት ሰዓት የቆረጠ ሰው ካለ ለምን አትይዙትም ራሳችሁ የተቃዋሚዎችን ስም ለማጥፋት የምታደርጉት የከሰረ ንግግር ነው በማለት እንደተቃወሟቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።