ምንጮቻችን ከአካባቢው እንደገለፁት በትግራይ
ክልል ምስራቃዊ ዞን ጉሎ-መኸዳ ወረዳ የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባላት የሆኑት ወገኖች በገዥው ስርአት ካድሬዎች በተቀነባበረ
ተንኮል ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጅት ጋር ግንኝነት አላችሁ እየተባሉ በሃሰት ምስክርነት እየታሰሩ እንደሚገኙ ለማወቅ
ተችሏል።
ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ በገዥው ስርአት እየታሰሩ ያሉት ሰዎች ህገ-መንግስታዊ
መብታቸውን ተጠቅመው በመቃወማቸው የተነሳ ያልተዋጠላቸው አስተዳዳሪዎች ለመጪው ምርጫ ተወዳዳሪዎች ሁነው እንዳይቀርቡ ሰለሰጓቸው
ሚያዚያ 3/ 2007ዓ/ም በውሸት ምስክረነት በፋፂ እስር ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት የሆኑ አቶ ይኩኖ አምላክና አቶ ሙሉ ለገሰ ከዛላምበሳና አካባቢው አቶ አሉላ
ክብሮምና አቶ ጌትነት ፀጋይ ደግሞ ከፋፂ ሲሆኑ ከወላጆቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለው እንደሚገኙ ምንጮቻችን
ጨምረው አስረድተዋል።